የውህደቱ ዓላማና አስፈላጊነት
ስለ አዲሱ ውህድ ፓርቲ በተሻለ ለመገንዝብ ይረዳ ዘንድአላማውና አስፈላጊነቱ እንደሚከተለው በስፋት ተተንትኖ ቀርቧል፡፡
የሳምንት መወያያ ርዕስ ላይም ስለ ውህደቱ ላነሳችው ስጋትና ጥያቄዎች በተወሰነ መልስ ይሆናችሁል፡፡
በተከታታይነትም ግልጽነት የመፍጠር ስራ ይቀጥላል፡፡
1. ግንባሩ ተልዕኮውን በማጠናቀቁ፣
ኢህአዴግ በሚመሠረትበት ወቅት የብሔር ጭቆናንለማስቀረትና የብሔር ጥያቄ ለመመለስ የተፈጠረስትራቴጂካዊ ግንባር ነው፡፡ የኢፌዲሪ ህገ-መንግስት ፀድቆውዲሞክራሲያዊና ፌደራላዊ ሥርዓት እውን ከሆነ በኋላ የብሔርብሔረሰቦች እራስ በራስ የማስተዳደር መብት፣ ቋንቋ፣ ባህልእና በማንነት የሚኮሩበት ህገ-መንግስታዊ መብቱ ተረጋግጧል፡፡ስለዚህ ግንባሩ የተፈጠረበት ዋንኛውን ዓላማ አሳክተዋልማለት ይቻላል፡፡ ብሄር ብሄረሰቦች በዚህ ህገ-መንግስት መነሻእራሳቸውን በራሳቸው ማስተዳደር መብት በመጎናፀፋቸውበሁሉም የአስተዳደር እርከኖች ይኸው ተግባራዊ ሆኗል፡፡የስርዓቱ ዋና መለያ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የራስንእድል በራስ የመወሰን ያልተገደበ መብታቸውን መሰረት ያደረገፌዴራላዊ የመንግስት አወቃቀር፣ አደረጃጀትና አሰራርማቋቋሙ ነው፡፡
በአብዛኛው የዓለም ተሞክሮ እንደሚያሳየው መሰልአደረጃጀቶች ማለትም (የግንባር፣ ንቅናቄ፣ ነፃ አውጭ ወዘተ) ባለው ሥርዓት ላይ በማመፅ በትጥቅ ትግል ወይም በሌላአግባብ የሚታገሉ ናቸው፡፡ ከዚህ አኳያ ኢህአዴግም የደርግስርዓት በትጥቅ በማስወገድ ህገ-መንግስታዊ ሥርዓትመመስረት ነበር፡፡ አደረጃጀቱ በዚያን ወቅት ተገቢ ቢሆንምላለፉት 27 ዓመታትም በዚሁ መቀጠሉ በተለያዩ ጉዳዮችአሉታዊ ተፅዕኖ ነበረው፡፡ ስለዚህ የግንባር አደረጃጀቱተልዕኮውን አሳክቶ የጨረሰ ብቻ ሳይሆን ከወቅቱ ነባራዊሁኔታ ጋር የማይራመድ በመሆኑ ወደ አንድ ወጥ ፖርቲመምጣት አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ጭምር ነው፡፡
2. አንድ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ማህበረሰብመፍጠር፣
ኢትዮጵያ የተለያዩ ብሄሮችና ሃይማኖቶች መገኛ ሆና ሳለ ይህንበአግባቡ ማስተናገድ ባለመቻሏ ብሄረ መንግስት ግንባታዋረጅም ጊዜን ወስዶባታል፡፡ የዚህ ዋነኛ ምክንት ደግሞ አንድየጋራ የኢኮኖሚና ፖለቲካ ማህበረሰብ የመፍጠር ሂደት ችግርመሆኑን በመለየት ህገ-መንግስቱ ሲፀድቅ ይህን ዓላማ መሰረትያደረገ ግብ እንዲቀመጥ ሆኗል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ይህን አንድ የፖለቲካ ማህበረሰብለመገንባት የወሰኑት በራሳቸው ፍላጎትና በነፃ ፈቃዳቸው ላይተመስርተው ነው፡፡ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችናሕዝቦች አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማህበረሰብ የመገንባትአላማቸው የሚሳካው ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶቻቸውሲከበሩ ብቻ ነው፡፡
አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ለመፍጠርየኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ትስስር የሚፈጥሩ ሀገራዊፕሮጀክቶችን መቅረፅና ተግባራዊ ለማድረግ እንዲሁምየኢኮኖሚያዊ ትስስሩ እንዲጠናከር የዜጎች በፈለጉት አካባቢየመንቀሳቀስ ነፃነት ያለምን ገደብ ሊረጋገጥ ይገባል፡፡
በህገ-መንግስቱ ላይ የኢትዮጵያ ህዝቦች ፍላጐት አንድ ጠንካራእና ዲሞክራሲያዊ ሀገር የመፍጠር ራዕይን እውን ለማድረግይህ አደረጃጀት አብሮ የማይጣጣም በመሆኑ መሪ ድርጅቱአንድ ሳይሆን አንድ የፓለቲካና የኢኮኖሚ ማህበረሰብ መፍጠርስለማይቻለው አንድ ወጥ ሀገራዊ ፓርቲ የመፍጠር አስፈላጊነትበእጅጉ የጐላ ያደርገዋል፡፡
3. ወቅታዊ የብሔር ፅንፈኝነት ጫፍ የረገጠመሆኑ ፣
በሀገራችን የቀድሞ ስርኣቶች የብሄር ብሄረሰቦች መብትአለመረጋገጥ ምክንያት ትግል ተካሄዶ ኢህአዴግ ደርግንበማስወገድ የእኩልነት መብት የሚሰጥ ህገመንገስትበመረጋገጡ የብሄር ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ የተደረገ ቢሆንምየብሄር መብትን ከአገራዊ አንድነት ጋር አጣጥሞ ባለመሄድምክንያት ብሄርተኝነት እየተስፋፋ አሁን ላይ ጫፍ የደረሰበትደረጃ ላይ እንገኛለን፡፡
ፅንፈኛ ብሄርተኝነት በዘመነ አለማቀፋዊነት ልዩነቶችንአቻችሎ ከአብሮነትና ከዴሞክራሲያዊ አንድነት ሊገኙየሚችሉትን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ባህላዊጸጋዎች ከማሳደግ ይልቅ በተቃራኒው ይጓዛል፡፡ በዚሁየጥርጣሬና የጥላቻ መንፈስ ከጋራ ልማቱ በጋራ መጠቀምእየተቻለ እንዳይሳካ ያደርጋል፡፡
በመሆኑም ህዝብን በድህነትና በኃላቀርነት የማስቀጠል አደጋያስከትላል፡፡ ፅንፈኛ ብሔርተኝነት አንዱን ከፍ ሌላውን ዝቅአድርጎ ከማየት የሚነሳ አደገኛ አስተሳሰብ ነው፡፡ የአንደኛውንመልማት የሌላኛው ድህነት አድርጎ የሚመለከት ነው፡፡የአንደኛው ህዝብ መብት መረጋገጥ የሌላኛውን መብትእንደሚነፍግ አድርጎ ይመለከታል፡፡ ይህም በመሆኑ ከመነሻውዴሞክራሲያዊ ውይይቶችን ቀርቅሮ ይዘጋል፡፡
ችግሮችን ሊፈታ የሚፈልገው በፀረ-ዴሞክራሲና በአፈናአግባብ ነው፡፡ ክርክሮችና ውይይቶች እንዲበራከቱአይፈቅድም፡፡ ዴሞክራሲያዊ ውይይት፣ የአብላጫ ወሳኝነት፣ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት የሚባሉ ነገሮችን አይቀበልም፡፡የስርዓት አልበኝነትና የፀረ-ዴሞክራሲያዊያን መንቀሳቀሻማዕከል ይሆናል፡፡
ፅንፈኝ ብሔርተኝነት ተሰባጥረው የሚኖሩ ህዝቦችንናአንድነታቸውን በጥላቻ ይመለከታል፡፡ በህዝቦቹ መካከልጥላቻና አለመተማመን እንዲሰፍን ይሰራል፡፡ በህዝቦቹ መካከልልዩ ልዩ ምክንያቶችን እየጫረ ደም አፍሳሽ ግጭት እንዲሰፍንያደርጋል፡፡ ህዝቦችን የሚያስተሳስሩ የአንድነት ገመዶችንእየለቀመ ይበጣጥሳቸዋል፡፡ ለዚሁ አላማው ማስፈፀሚያአስፈሪና አሰቃቂ የሆኑ ጭፍጨፋዎችን ጭምር ያካሂዳል፡፡
ፅንፈኝ ብሔርተኝነት ከየትኛውም አቅጣጫ ይነሳ አንድየኢኮኖሚና የፖለቲካ ማህበረሰብ የመገንባት እሳቤን ተፃርሮየሚቆም ነው፡፡ ብዝኃነት በሰፈነበት ሁኔታ አንድ የኢኮኖሚናየፖለቲካ ማህበረሰብ ተገነባ ማለት ማንኛውም አይነት የፅንፈኝብሔርተኝነት እድሜው ያጥራል ማለት ነው፡፡ የጋራ ልማትናየጋራ ተጠቃሚነት በሰፈነ ቁጥር አክራሪ አስተሳሰቦች ቦታያጣሉ፡፡ ይህም በመሆኑ አንድ የኢኮኖሚና አንድ የፖለቲካማህበረሰብ ለመገንባት የሚካሄደውን ጥረት በሙሉእየተከታተለ ለማጥፋትና ህብረትን ለማፍረስ ይሰራል፡፡
በብሄር ከመደራጀት ወደ ውህድ ፓርቲ በመሸጋገር የብሄርፅንፈኝነት ከሚፈጥሩ ምቹ መደላድሎችን በማሳጣትመቀጨጭ የሚያስችል እድል ይፈጥራል፡፡
ስለሆነም ጽንፈኝነት ጊዜው ያለፈበት መሆኑን ለህብረተሰቡግንዛቤ የመፍጠር ሥራ በመስራት የሚዲያና የሃማኖትአባቶች ተሳትፎ በማሳደግ፣ መንግስትም ነፃ የሆነ አስተዳደርበመመስረት እራሱን ዲሞክራሲያዊ ህብረ-ብሔራዊ ኢትዮጵያየቆመ መሆኑን በማስመስከር፣ ተገቢውን ህግ በማውጣትናበማስፈፀም፣ ህዝባዊ ዕርቅ በመፈፀም፣ ፍትህን እኩልተጠቃሚነትን በማስፈን፣ መንግስት ይቅርታ በመጠየቅ፣ ህዝብእርሰ በርሱ ይቅርታ እንዲጠያየቅ ሁኔታዎች መመቻቸትአለባቸው፣ የሀገር አንድነትን በመስበክ፣ ሁሉም አቀፍ የሆነልማት በማምጣት፡ ብሄሮች ብሄረሰቦች እና ህዝቦች መካከልጥሩ ግንኙነት እንዲኖር ዕድል በመፍጠር ዴሞክራሲያዊብሄርተኝነትን ከሀገራዊ አንድነት ጋር ተጣጥሞ እንዲጎለብትበማድረግ፣ ልዩነታችን ውበታችን መሆኑን ማስተማር፣ ፅንፈኛብሄርተኝነት ላይ ጉዳቱን ማስተማር እና መልካም አስተዳደርእንዲኖር ማድረግ ይገባል፡፡
ስለዚህ አደረጃጀቱ ሁሉንም የሚያሳትፍ በሆነ አግባብ አንድወጥ ሀገራዊ ፓርቲ መመስረት ወቅታዊና ተገቢ ያደርገዋል፡፡
4. ፌዴራል ስርአቱ እና የፓርቲ ውህደትተያያዥነት የሌላቸው መሆኑ ፤
ሀገራችን ኢትዮጵያ ህገመንግስቱን መሰረት በማድረግየምትከተለው የፌዴራል ስርዓት መሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚህመሰረትም ዘጠን ክልሎች የተዋቀሩ ሲሆን እነዚህን ክልሎችመሰረት በማድረግም ብሄራዊ ድርጅቶች እየመሯቸው ይገኛሉ፡፡በፌዴራላዊ ስርዓት እያንዳንዱ ክልል የራሱ ድርጅት ይኑረውየሚል አሰራርም ሆነ ህግ የሌለ ሲሆን በዓለም አቀፍ ደረጃምየፌዴራል ስረዓት የሚከተሉ አገራት ልምድም ይህን አያሳይም፡፡ስለሆነም ብሄራዊ ድርጅት መኖርና የአገራችን ፌዴራል ስርዓትየተሳሰሩና የግድ የሚል አይደለም፡፡
አንድ ወጥ ሀገራዊ ፓርቲ መፍጠር ማለት ፌደራላዊ ሥርዓቱጋር ምንም የሚያጋጨው ነገር ፈፅሞ የለም ፡፡ በጣም ግልፅመሆን ያለበት ዐቢይ ጉዳይ ቢኖር ፓርቲን አንድ እናድርግ ሲባልበህገ-መንግስቱና በፌደራላዊ ሥርዓቱ ማዕቀፍ ብቻ ነው፡፡ምክንያቱም ኢህአዴግና አጋሮቹ ብቻ ህገ-መንግስቱንም ይሁንፌደራላዊ ሥርዓቱን መቀየር አይችሉም፡፡ ይህ የመላውየኢትዮጵያ ህዝብ ውሳኔ ነው የሚሆነው፡፡ በሌላ በኩልኢህአዴግና አጋሮቹ ወጥ ፓርቲ የሚሆኑት ፌደራሊዝሙንለማፍረስ ሳይሆን ጠንካራ ዴሞክራሲያዊ ፌደራዝም እውንለማድግ ነው፡፡ ይህ ማለት ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚሳተፍበትበእኩል የሚወሰንበት፣ ፍትሃዊ እና አካታች የፖለቲካ ውህደትለመፍጠር ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ የብሔር ማንነትና የጋራማንነትን በአግባቡ አስታርቀው ለማስተናገድ ነው፡፡
ይህ ብዥታ ከሁለት መሠረታዊ መነሻ ሊነሳ ይችላል፡፡ አንደኛውከዚህ በፊት የነበረው የኢህአዴግና አጋሮቹ አደረጃጀት በብሔርማንነትን መሠረት ያደረገ ሲሆን ፌደራሊዝሙም ከዚሁ ጋርየሚሄድ የፓርቲው አደረጃጀት ሲለወጥ ፌደራላዊ ስርዓቱሊለወጥ ይችላል በሚል የውሁደቱን አጠቃላይ ይዘትካለመረዳት የሚመነጭ ሲሆን ይህ ውይይት በሚደረግበትወቅት የፓርቲ ውህደትና የፌደራሊዝም አደረጃጀት ጋር ምንምዓይነት ግንኙነት እንደሌለው እንዲያውም በፌደራሊዝም ላይየሚነሱ ጉድለቶችን በተሻለ ደረጃ በማረም ማስቀጠል መሆኑንሲረዱ ግልፅ መሆን የሚችል ነው፡፡
በአለም ላይ ያለውም ተሞክሮ እና ልምድ ሁሉም ፌደራሊዝምየሚከተሉ ሀገር የብሔር ማንነት ላይ የተመሠረተ የፖለቲካፓርቲዎች ወይም በየክልሉ ብቻ የሚንቀሳቀሱ ፖርቲዎቸየሉም፡፡ ሥርዓቱ ፌደራላዊ አወቃቀር ኖሮት ሲያበቃ ፓሪቲዎቹግን ሀገራዊ ፓርቲዎች ናቸው፡፡ የእኛም የውሁደት አካሄድዓለም አቀፍ ልምድን ከግንዛቤ የወሰደ የብሔር ማንነትና የጋራማንነትን በተሳካ አግባብ አስታርቀው ፌደራልዝሙን በተሻለለማስቀጠል ነው፡፡
ሁለተኛው ምክንያት ውሁደቱ እንዳይሳካ በብሔር አጥርውስጥ ተሸጉጠው የተጀመረው ሀገራዊ ለውጥና ተስፋእንዳይቀጥል ማንኛውንም መልካም ነገር ህዝብ በጥርጣሬእንዲመለከተው የሚሠሩ ሀይሎች ናቸው፡፡ እነዚህንለማስረዳት ጊዜ ማቃጠል አይገባም ይልቁንም ውሁደቱንበማፋጠን በተጨባጭ አሉባልታውን ማምከን ነው፡፡
እራስን በራስ የማስተዳደርና የብሔር ብሔረሰቦች መብትንበሚመለከትም ከውህደቱ ጋር ብዥታ ለመፍጠር የሚሞክረውሌላው ገፅታ ነው፡፡ እዚህ ላይ ቀደም ተብለው እንደተገለፀውየውሁደቱ ዋናው ዓላማ በተደጋጋሚ እንደተገለፀው የብሔርማንነትና የጋራ ማንነትን በእኩል የሚስተናገዱበት ውሁድለመፍጠር ነው ሲባል የብሔር ብሔረሰቦች ራሳቸውንማስተዳደር ህገ-መንግስታዊ መብት የተቀበለ ብቻ ሳይሆንበጥብቅ የሚያከበር ነው፡፡ የድርጅት መዋቅርና መንግስታዊመዋቅር ልዩነት በግልፅ የተሠመረ ነው፡፡ አዲሱ ውሁድ ፓርቲከሁሉም ብሔር ብሔረሰብ ስለሚያካትት በምርጫው ድርጅቱበየአካባቢው ብሔር ተወካዮችን በህዝሁ ተቀባይነትንያተረፉትን ያቀርባል ህዝብ በምርጫ ሲመርጠው እዚያውየራሱን አካባቢ ያስተዳድራል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ከዚህ ጋርተይዘው ልክ እንደ መጀመሪያ ነጥብ የብዥታ መነሻ ያለውሲሆን መረዳትም ያለብን ከላይ በተቀመጠው አግባብ መሆንይኖርበታል፡፡
ሌላው የብዥታ ገፅታ ደግሞ ከቋንቋ ጋር የተያያዘ ነው፡፡በጥናቱ መሠረት የፓርቲው የሥራ ቋንቋ ‘'multi lingual‘' ወይም በርካታ ቋንቋዎች ሲኖሩት በየአካባቢው የሚነገረውቋንቋ እና በሀገር ደረጃ ለሥራ ቋንቋነት ከተመረጡት ያሻውንወስደው ይሠራል ማለት ነው፡፡
ሰለዚህ ቋንቋዎችን የሚያቀጭጭ ሳይሆን እንደውም በሀገርደረጃ ፓርቲው የሥራ ቋንቃዎችን በርካታ በማድረግ ቋንቃዎቹይበልጥ እንዲያደጉ እድል ያጐናፅፋቸዋል፡፡ ስለዚህ ከተራቁጥር 1 እስከ 3 ያሉትን ከጥሬ ሀቁ እጅግ የራቁትን የሀሰትመረጃዎችን በመታገልና በማገለጥ ወደ ውሁደቱ ትኩረትልንሰጥ ይገባል፡፡
5. አጋር ድርጅቶችን አግላይ የነበረ መሆኑ
የኢህአዴግ አደረጃጀት በአራት ክልሎች በሚገኙ አባል ብሄራዊድርጅቶች በመያዝ የተመሰረተ ነው፡፡ ግንባሩ አጋር ድርጅቶችያላቀፈ በመሆኑ በሀገሪቱ ወሳኝ የፖለቲካ ውሳኔ ላይ አምስቱንክልሎች የሚመሩ አጋር ድርጅቶችን የማያሳትፍ እና አካታችያልሆነ አደረጃጀት ነው፡፡
ይሁንና እነዚህ ድርጅቶች በውሳኔው ሂደት ሳይሳተፉ ነገር ግንየኢህአዴግን ውሳኔ የሚተገብሩበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ በውሳኔሂደት ክልሎችን ተጨባጭ ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ ውሳኔእንዲተላለፍ በማድረግ ክልሎቹ በልማትና በዴሞክራሲ ስርኣትግንባታ መድረስ ከሚገባቸው ደረጃ እንዳይደርሱ የራሳቸውውስጣዊ ሁኔታ እንደተጠበ ሆኑ አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነው፡፡
ከዚህም የላቀው ጉዳይ በሀገራዊ ጉዳይ እኩል የሚመክሩበትእድል ማነሱ ለሀገራቸው ባይተዋርነት ስሜትእንዳይፈጥርባቸው በተለያየ ጊዜ ወደ ግንባሩ አባል ለመሆኑተደጋጋሚ ጥያቄዎችን በማቅረብ ትግል ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡አደረጃጀቱ አካታች ካልሆነ ከፌደራላዊ ሥርዓቱ ጋር የሚጋጭመሆኑ ግልፅ ነው፡፡ ስለሆነም አነድ አገራዊ ድርጅት ቢኖርበነዚህ ክልሎች ያለ መንኛውም ዜጋ በሌሎች ክልሎች ካሉዜጎች እኩል የመሳተፍ እድልን የሚያሰፋና ፍትሃዊና ሚዛናዊውክልናን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል፡፡ ስለሆነምአደረጃጀቱ ሁሉንም የሚያሳትፍ በሆነ አግባብ አንድ ወጥሀገራዊ ፓርቲ መመስረት ወቅታዊና ተገቢ ያደርገዋል፡፡
6. የኢህአዴግ ጉባኤ ያስቀመጠው አቅጣጫመፈፀም ድርጅታዊ ዲስፒሊን መሆኑ፡-
በ11ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ ባደረገው ውይይት በግንባሩ ቀጣይእጣፋንታ ላይ ውሳኔ ለመወሰን ባስቀመጠው እቅጣጫመሰረት ጥናትን መሰረት በማድረግ አባል ድርጅቶች ውህደትእንዲፈጥሩ እና በዚህ ውደትም አጋር ድርጅቶች ጋር ያለንስትራቴጂካዊ ግንኙነትም በጥናት ላይ ተመስርቶ ምላሽእንዲሰጠው መወሰኑ የሚታው ነው፡፡ ስለሆነም ይህ ድርጅቱንከግንባር ወደ አንድ ድርጅት ውህደት መፍጠር መነሻውድርጅታዊ ጉባኤው ያስመጠው አቅጣጫ በመሆኑ ተፈፃሚእንዲሆን በድርጅታዊ ዲሲፒሊን ሁሉም ሊያከናውነው የሚገባጉዳይ መሆኑ መዘንጋት የለበትም፡፡
7. ለቀጣዩ ምርጫ ኢህአዴግ በአዲስ መልክራሱን ሪበራንድ በማድረግ ትልቅ ፋይዳ አለው፡፡
አንድ የፖለቲካ ድርጅት በህዝብ ምርጫ ወደ ስልጣንለመምጣት የሚሰራ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ በምርጫ ለማሸነፍፖለቲካ ድርጅቶች የተለያዩ ስልቶችን የሚጠሙ ሲሆን ይህምየህዝብን ይሁንታ ለማግኘት ጥቅም ላይ የሚያውሉት ነው፡፡በሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ኢህአዴግ የሰራቸው እጅግአበረታች እና አመርቂ ለውጦችን ማምጣት የመቻሉን ያህልበህዝቡ ዘንድ እንዲጠላ የሚያደርጉ ከሰብዓዊ መብቶችናፍትሃዊ ልማት ከማረጋገጥ አንፃር ብሎም ኪራይ ሰብሳቢነትንአለመድፈቅ ችግር እንዳለ በለውጡ ዋዜማ መገምገማችንየሚታወቅና ህዝቡም በተለያየ ሁኔታ መግለፁ የሚታወስናሀገራችንን ምን ያህል አደጋ ተፈጥሮባት እንደነበር የቅርብ ጊዜትውስታ ነው፡፡
ስለሆነም በባለፈው አንድ ዓመት በተለያዩ ዘርፎችባስመዘገብነው ለውጥ ህዝቡ ጋር መግባባትን እየፈጠርንሲሆን ይህን የድርጅታችንን ስያሜ እና ማኒፌስቶ ለውጥበማድረግ በዴሞክራሲና ሰብዓዊ መብት ላይ ስር ነቀል ለውጥለማማጣት የሚሰራ ድርጅት መሆኑን በማስገንዘብ ሪብራንድበማድረግ የበለጠ ህዝባዊ ቅቡልነታችንን ያስረግጥልናል፡፡ ይህህዝባዊ ቅቡልነታችን ደግሞ በምርጫ 2012 የምንፈልገውንግብ ለማሳካት የሚኖረው አወንታዊ አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነው፡፡ስለሆነም ውህደት መፍጠሩ ለሪብራንዲን አንዱ ማሳያ ሆኖሊታይ የሚችል በመሆኑ አስፈላጊ ያደርገዋል፡፡
8. የውህደቱ ጊዜው አሁን መሆኑ
በሀገራችን በተፈጠረው ለውጥ የፖለቲካ ምህዳሩ መስፋትተከትሎ የተለያዩ ፖለቲካ ሃይሎች በመሰባሰብ ጠንካራ ፓርቲለማቀቀም እየተንቀሳቀሱ የሚገኙበት ወቅት ላይ እንገኛለን፡፡
በዚህ ሂደት ኢህአዴግም አደረጃጀቱን ፈትሾ ተጠናክሮካልወጣ ስተቀር የመሪነት ሚናውን አደጋ ላይ የሚጥሉሁኔታዎችም እየተፈጠሩ ይገኛል፡፡ ስለሆነም ድርጅታችንከሀገራዊ ነባራዊ ሁኔታዎችን በማየት እራሱን አጠናክሮለመምጣት ያለው ዕድል ከላይ በዝርዝር እንዳየነው አንድውህድ ፓርቲ ሆኖ መገኘት በእጁ ላይ የሚገኝ ትልቅ ዕድል ሆኖይገኛል፡፡ ውህድ ፓርቲ ሆኖ መምጣትን እንደትልቅ ዕድል ከታየደግሞ ጊዜው ነገ ወይም ወደፊት ሳይሆን አሁን ነው፡፡
9. ሚዛናዊ ውክልና ፣
አንድ ውህድ ፓርቲ መሆኑ ከሚያስገኘው ጥቅም መካከል አንዱየሆነው በሁሉም አካባቢ የሚኖሩ ዜጎችን ያለምንም ክልከላበአደረጃጀቱ የሚሳተፉበት አካታችና ፍትሃዊ ውክልና እንዲኖርየሚያስችል መሆኑ ነው፡፡ ይህም በአንድ አካባቢ የሚኖርማንኛውም ዜጋ በዚህ ውህድ ድርጅት የእከሌ ብሄር ካልሆነየሚል ክልከላ ሳይኖርበት በሚኖርበት አካባቢ መደራጀትየሚችልበት ሁሉን አካታች ፍትሃዊ ውክልናም እንዲኖርየሚያስችል ይሆናል፡፡
10. የአስተሳሰብና የተግባር አንድነትን የማጠናከር አስፈላጊነት፣
ድርጅታችን ኢህአዴግ በየጊዜው በውስጡ በሚፈጠሩከመስመር መውጣት ምክንያት ለከፍተኛ ችግሮች ራሱንናአገሪቱን ሲያጋልጥ መቆቱ የሚታወስ ነው፡፡
በተጨማሪም ከጊዜ ወደ ጊዜ በኢህአዴግ እህት ድርጅቶችመካከል መጠራጠር፤ መገፋፋት፤ መቃረን እየበረታ መምጣቱናእያንዳንዱ ብሄራዊ ድርጅት እና አመራሩ በሚሰራቸውስህተቶች ከመታረም ፈንታ ወደ ብሄራዊ ድርጅቶች ጉያእየተወሸቁ ጥፋትን ሰበሰብ እየሰጡ መጓዝ፤ ድርጀቱ ከጊዜወደ ጊዜ የክሰተት መሪ እንጂ አርቆ አሳቢነት እየራቁትመምጣታቸው በብሔራዊ ድርጅቶች መካከል እርስ በርስየመጠራጠርና ለተሟላ ትግል የማያመች በመሆኑ ሁሉምበድርጅታዊ ነፃነት ሽፋን የብሔር ምሽግ እየጠነከረየሚሄድበት ዝንባሌ ስለሚታይ ይህንን በማስቀረት በመርህናበድርጅት ዓላማ መሠረት በማድርግ ለመተራረም እና ወጥየአስተሳሰብና የተግባር አንድነትን ለማረጋገጥ ወደ ውህደትማሸጋገር ተፈላጊ ያደርገዋል፡፡
ይህ ውህደት ሲፈጠር አባል ድርጅቶች ውህደቱን የሚፈጥሩትበፕሮግራም ተመሳሳይነት ያላቸው በመሆኑ የሚፈጠሩችግሮችን ትግል ለማድረግ እና በብሄራዊ ድርጅት የመታጠርንካባ የሚያወልቅ የህግ የበላይነት እንዲሰፍን የሚስችል ምቹሁኔታን የሚፈጥር በመሆኑ ዴሞክራሲያዊ ማእከላዊነትንበማስጠበቅ ጠንካራ ፓርቲ እንዲሆን ያስችላል፡፡
No comments:
Post a Comment